በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኢጣሊያና አካባቢው ሀገረ ስብከት አጀማመርና አወቃቀር ።

  • በጥቅምት 2011 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ስብሰባ አመዳደብ መሠረት ኢጣሊያ/ጣሊያን፣ ፍረንሳይ፣ ቤልጂየም፣ ግሪክና ቱርክን አምስቱን ሀገሮች አቅፎ የኤጣሊያና አካባቢው ሀገረ ስብከት እንዲባልና በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ እንዲመራ ተደረገ።
  • በዚሁ ከላይ በጠቀሰው ዓመት በጥር ወር በሀገረ ስብከቱ ሥር ከሚገኙት 18 አብያተ ክርስቲያናት ሁለት ሁለት ተወካዮች  ሮማ ደረስ እንዲመጡ ተደርጎ የሀገረ ስብከት ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ስብሰባ ተካሄደ፤ በዚህ ታሪካዊና የመጀመሪያ ስብሰባ ከተሠሩት ሥራዎች አንዱ የሀገረ ስብከቱን የአስተዳደር ጉባዔ አባላት ማስመረጥ ነበረ። በምርጫውም፦

           1/  መ/ሕይወት ቀሲስ ፍሥሐ  ድንበሩ                          ዋና ጸሐፊ
           2/  መ/ኃይል አባ ወ/ ሰንበት ተ/ማርያም                        የሰበካ /ጉ/ማደራጃ ሐላፊ
           3/  መ/ሣህል አባ ወ/ ዮሐንስ  አጥናፉ                           ገንዘብ ያዥ
           4/  መ/ ምህረት አባ ኤርምያስ   ገድሉ                           ስብከተ ወንጌልና የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ ሐላፊ
            5/  ዲ/ን መስፍን ኀይሌ                                             ሂሳብ ሹም
            6/  አቶ ሚካኤል ማሪኖ                                             ም/ጸሐፊ
            7/  መ/ምህረት አባ ክንፈ ሚካኤል                               የካ/አስተዳደር
       እነዚህ የሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባዔ አባላት ሁነው ተመረጠው በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነት የሀገረ ስብከቱ ሥራ እየተሠራ ቆይቷል።
በ2013 ዓ/ም  በአስተዳደር ጉባዔው ውስጥ የተደረጉ ለውጦች።  

በ2013 ዓ/ም  በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚመሩ ሀገሮችን በተመለከተ የተደረገ ለውጥ።

በ2013 ዓ/ም የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ ግሪክ ወደ ስዊድንና አካባቢው ሀገረ ስብከት እንዲሔድ ተደርጎ ማልታና ስፔይን ተካተውበት ኢጣሊያ ፈረንሳይ ቤልጂየም ቱርክ ማልታና ስፔይን እነዚህን ስድስቱን ሀገሮች አቅፎ የኢጣሊያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ተብሎ ለውጥ ተደርጓል።
በ2012 ዓ/ም በፈረንሳይ 2 አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ተተክለዋል፤ የማልታና የስፔይን ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ተጨምረዋል። ከላይ ከተጠቀሱት 18 አብያተ ክርስቲያናት ግሪክ ሲቀነስ 17 በጠቅላላው 21 አብያተ ክርስቲያናት በሀገረ ስብከቱ ሥር ይገኛሉ።
 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!